የማርኬቲግ ባለሙያ

Part Time Temporary
Share it, to your Friends

  • Part Time
  • Temporary
  • Ethiopia
  • Applications have closed

AmazonEthiopia

የስራ ዝርዝር

ዋና ስራው በአማዞን ኢትዮጵያ የሻጭ (ሊሸጡ የሚችሉ ነጋደዎችን) እና የገዥ ቁጥር መጨመር ሲሆን የሚከተሉት ዝርዝር  ተግባራት ይኖሩታል።

  1. በሚኖሩበት ከተማ የሚገኙ አምራች ኩባንያዎች፣ አከፋፋይ እና ቸርቻሪ ነጋደዎች በአማዞን ኢትዮጵያ አካውንት እንዲከፍቱ እና እንዲሸጡ ማድረግ
  2. ነጋደዎች በአማዞን ኢትዮጵያ ( በኦንላይ ሽያጭ) የሚያገኙትን ጥቅም በማስረዳት እንዲሸጡ ማሳመን
  3. ለሻጭ ነጋደዎች የቴክኒካል ድጋፍ ማድረግ
  4. ለሚሸጡ እቃዎች ገዥ ማፈላለግ
  5. የድርጅቱን የማርኬቲንግ አሰራር ለማዘመን አዳዲስ አሰራሮችን መዘርጋት፣ክፍተቶችን እየለዩ ማሳወቅ እና አቅጣጫ ማሳየት
  6. ከአማዞን ኢትዮጵያ ሻጮች እና ገዥዎች ጋር ተግባብቶ መስራት እና ማማከር
  7. ከሰራተኞች እና ደንበኞች የሚሰጡ አስተያየቶችን መተንተን
  8. በተለያዩ መንገዶች (በድረ ገጽ እና በቪድዖ) የሚሰጡ ስልጠናዎችን መከታተል እና ወደ ውጤት አምጭ አሰራር መቀየር
  9. የአማዞን ኢትዮጵያ ማስታወቂያዎችን ፣ ባነሮችን፣ ጽሁፎችን ፣ ስዕሎች፣ …. በተገቢው መንገድ መረዳት እና ለደንበኞች ማስረዳት
  10. ሌሎች ከስራ አስጊያጅ እና ባለሙያዎች የሚሰጡ ስራዎችን መስራት

1.     የመወዳደሪያ መስፈርቶች እና ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው

  1. ከአሁን ቀደም ማህበራዊ ሚዲያን ( ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ቴሌግራም፣ ቲውተር፣ ሊንክዲን፣ ቲክቶክ፣ ፒንትረስ …) በደንብ የተረዱ መሆን አለባቸው (ማህበራዊ ሚዲያን የሚያስተዳዲሩ ቢሆን ይመረጣል)
  2. አማዞን ኢትዮጵያ (com) ድረገጽን የሚያውቁ እና የሚሰጣቸውን ስልጠና በፍጥነት የሚረዱ
  3. የትምህርት ዝግጅት 10ኛ ክፍል እና በላይ የሆኑ
  4. እንግሊዝኛ እና አማርኛ ቋንቋ በደንብ የሚችሉ፤ በተጨማሪም ሌሎች ቋንቋዎችን ማለትም ኦሮሞኛ፣ ትግርኛ፣ አፋረኛ ፣ ሶማሌኛ ….. ወዘተ የሚችሉ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።
  5. አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን፣ አሰራሮችን እና ፈጠራዎችን ለመማር ዝግጁ የሆኑ
  6. ከሰዎች ጋር ተግባብቶ የመስራት ፣ የአመራር ብቃት፣ ችግር የመፍታት እና የራስ መተማመን ብቃት ያላቸው
  7. ጾታ አይለይም። ሴቶች ይበረታታሉ።

2.    የስራ ሁኔታ እና ባህሪያት

  • ስራው የትርፍ ሰዓት ስራ ሲሆን በ24 ሰዓት ውስጥ የትም ቦታ ሆነው፤ በመረጡት ሰዓት የሚሠራ ነው።
  • ሰራተኛው የራሱን ኮምፒውተር ወይም ሞባይል ተጠቅሞ በራሱ የኢንተርኔት ወጭ የሚሰራ መሆን አለበት።
  • በቀን የተሰራው ስራ በ24 ሰዓት ውስጥ (ከ 5 ደቂቃ ባልበለጠ በድምጽ ወይም በአጭር ጽሁፍ) ሪፖርት መደረግ አለበት።
  • የመጀመሪያው ወር የሙከራ ጊዜ ሲሆን የሚከፈለውም ኮሚሽን እና ደመወዝ በግማሽ ነው።
  • በመጀመሪያው ወር ጥሩ አፈጻጸም ካላሳየ ውል ይቋረጣል።
  • ስለስራው ሙሉ ስልጠና ይሰጣል።
  • ጥሩ አፈጻጸም የሚያሳዩ ከኮሚሽን በተጨማሪ በወር ከ 30 ሽህ በላይ ተከፋይ እና ቋሚ የአማዞን ኢትዮጵያ ሰራተኛ ሊሆኑ ይችላሉ።

3.    ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም

  • በየወሩ የሚከፈል ቋሚ ደመወዝ እና በሰሩት ልክ ኾሚሽን የሚከፈል ሲሆን የብሩ መጠን በስምምነት ይሆናል።
  1. የመመዝገቢያ ሁኔታ

ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች እስከ ግንቦት 15፣ 2016 የሚከተለውን ሊንክ በመንካት የተጠየቁትን መስፈርቶች በጥንቃቄ በማንበብ ማመልከት ትችላላችሁ።

https://forms.gle/7bRFUjkAiqqB4Hde6

 


Share it, to your Friends