በቦሌ ክፍስ ከተማ ወረዳ 15 የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

Share it, to your Friends


አዲስ አበባ አስተዳደር ቦሌ/ከ/ከተማ/መ/15/ፋ/ጽ/ቤት ግልጽ ጨረታ በማውጣት የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ,
በመሆኑም በጨረታው ስመሳተፍ፡

  1. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ
    መለያቁጥር ሰርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የባት 1 ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቶች ለሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ሎት 1-2
    የፅዳት ዕቃዎች ብር 5,000 000፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሠዓት እስከ ቀኑ አስር ሠዓት ድረስ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00/ሃምሳ ብር/ ሃያት አደባባይ ዙሪያሽ ሞል 5ኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ. 504 ግዥ ቡድን በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ (Enancial documents) ዋናና ቅጅ (original and copy) [ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በወጣ 1ኛው የ ሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  6. የጨረታው አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበርያ 10% በማስያዝ ጨረታው በተከፈተ በ7ኛው ቀን በወረዳው ግዥ ቡድን ቢሮ • በአካል ቀርበው ውል መግባት አለባቸው፡፡
  7. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ተሸናፊ ተጫራቶች በእኩል ጊዜ በጽሑፍ በወረዳው የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ ይገለጣል፡፡
  8. በጨረታ ተሳታፊ የሆኑ ድርጅቶች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ 3 ቀን ቀድመው ለጽ/ቤቱ ማቅረብ አለባቸው::
  9. ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
    ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥርት፡- 01 8931909 ግዥ| ቡድን ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
    በቦሌ ክፍስ ከተማ ወረዳ 15 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

Share it, to your Friends

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *